Mn Alegn
Meskerem Getu
6:14አንተ የዘመናት አምላክ ያው አንተ ነህ አንተ አትለዋወጥም ያው አንተ ነህ እኔ እኔ ነኝ ያልህ ያው አንተ ነህ አንተ ትናንትናም ዛሬም ያው አንተ ነህ አለም ተለዋዋጭ ሁሉ ሲቀያየር ከፍ ያለው ዝቅ ሲል የነበረው ሲቀር ፍሰቱን ጠብቆ ሁሉ ሲተካካ አንተ ፀንተህ ኗሪ ምንም ሳትተካ የማትለዋወጥ አንተ ብቻ ዘመን የማሽርህ አንተ ብቻ የነበርህ ያለህ አንተ ብቻ ዙፋንህ የፀና አንተ ብቻ ክበር ክበርልን ንገስ ንገስ ሙሉ መስዋዕታችን ላንተ ይፍሰስ ብርቱዎች ሲደክሙ ደካሞች ሲገዙ ሽማግሌው ሲያልፍ ሲያረጅ ጎበዙ ዕውቀትም ሲሻሻል ስልጣኔ ሲሻር አንተ ለዘላለም ተረጋግተህ የምትኖር