Notice: file_put_contents(): Write of 645 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Meskerem Getu - Minim Ayisanihim | Скачать MP3 бесплатно
Minim Ayisanihim

Minim Ayisanihim

Meskerem Getu

Альбом: Ya Messih
Длительность: 5:41
Год: 2024
Скачать MP3

Текст песни

አንተን ተስፋ አድርጌ መጥቼ ነበረ
ፀሎቴን ሰምተሃል ስለቴ ሠመረ
ፀሎትን ትሰማለህ እንባንም ታብሳለህ
ለሚጠሩህ ቅርብ ነህ ደጅህን ትከፍታለህ

ኡ አንዳንድ ጊዜ እታወካለሁ
የሚነፍሰው ነፋስ ታንኳየን ሲንጠው
ኡ መርከቤ ላይ ጌታዬ ተኝተህ
ይሄ ሁሉ ሲሆን አታይም ወይ ነቅተህ
የሚሆነው ሳይገባኝ ተጨንቄ ሳምጥ
ታንኳዬ በውሃ ሲሞላ ስናወጥ
ማዕበል የሚታዘዝህ የሚሰማህ ወጀቡ
በተነሳህ ጊዜ ያወኩኝ ዝም አሉ

ምንም ምንም አይሳንህም
የማመልክህ ጌታ ትችላለህ ሁሉንም

ኡ ባለመድሃኒት ያልተገኘላት
አስራሁለት አመት ደም እየፈሰሳት
ኡ ተንከራታች ያላትን ሁሉ አጥታ
ማንም አልተገኘም ችግሯን የሚፈታ
ከህዝብ ሁሉ መሀል በእምነት ተጋፍታ
ፈውሷን  ተቀበለች የልብሱን ጫፍ ነክታ
ለስንቱ መለኛ ላዋቂ ያቃተ
ድንቅ መካር ሃያል ቀላል ነው ለአንተ

ምንም ምንም አይሳንህም
የማመልክህ ጌታ ትችላለህ ሁሉንም

ኸረ  ምንም ምንም አይሳንህም
የማመልክህ ጌታ ትችላለህ ሁሉንም

ኸረ  ምንም ምንም አይሳንህም