Che

Che

Michael Belayneh

Альбом: And Qal Concert
Длительность: 5:28
Год: 2025
Скачать MP3

Текст песни

ቼ ካሉ በኁዋላ
የምን ማለት ወደኁዋላ
የምን መለስ ቀለስ
ቼ ብለን ከወሰን መድረስ

በሕይወት ምኅዋር በረቂቅ መንገድ
በዕምነት ሀ ያልነው የእኔና አንቺ መውደድ
በቃል ተወጥኖ በተስፋ ተክኖ
በልባችን ማሣ ቅንጣት ዘሩን ጥሎ
ድምጹን ሰውሮ ጠፍቶ እንዳልነበረ
እንደ በጋ መብረቅ ተግ ይል ጀመረ
በብርሃን ፈረስ ፍቅር ካሰገረን
እፍ ማለት እንጂ ምን አንገራገረን

ቼ ካሉ በኁዋላ
የምን ማለት ወደኁዋላ
የምን መለስ ቀለስ
ቼ ብለን ከወሰን መድረስ

ጸዳሉን ሊያለብሰን ፍቅር እየጠራን
ሀሁን እንከተል እንጂ ምን አስፈራን
የመውደድ ትንሣኤ ዳግም ካዋሐደን
ፈረሱ ላይ ወጥተን ካሰበው ይውሰደን

በቃል ኪዳን ልጉዋም ቼ ፍቅር ፈረሴ
በሐሴት ይስገሩ ነፍስሽና ነፍሴ
ፍቅር ካበጀልን ከእርስታችን ዐምባ
ዕምነት እየመራን ነይ ሰግረን እንግባ

ቼ ካሉ በኁዋላ
የምን ማለት ወደኁዋላ
የምን መለስ ቀለስ
ቼ ብለን ከወሰን መድረስ
ግላሱን ቆንጥጠን ሚዛኑን ጠብቀን
በእጃችን መቀነት እቅፉን አጥብቀን
ሰምረን ከፈረሱ
ሆሆሆ
መንጎድ እንጂ መልሱ
ሆሆሆ
የድል መባቻ ነው ዕምነትና ጽናት
የጀግና ሙያ ነው ወደ ንጋት ማቅናት
ሰው እና ሰው ሆኖ
ሆሆሆ
መኖር ፍቅርን ታምኖ
ሆሆሆ
ሰምረን ከፈረሱ
መንጎድ እነጂ መለሱ

ቼ ካሉ በኁዋላ
የምን ማለት ወደኁዋላ
የምን መለስ ቀለስ
ቼ ብለን ከወሰን መድረስ