Che
Michael Belayneh
4:38ወጣሁ ወረድኩልሽ ኩታበር ገራዶ አይጨበጥ ነፋስ ልቤ አንቺን ወዶ ወዴት ነሽ ጀግንዬ ኮምቦልቻ ነሽ ደሴ መርሳ ነሽ ወልዲያ ቦረና ከሚሴ የሠርክ ርኃቤ የሁልጊዜ ጥሜ እቅፍሽ ውስጥ ኾኜ የሚሞቀው ደሜ አብረውሽ የት ኼዱ ውርጭ ኹኗል ዙሪያዬ ሊገድለኝ ነው ብርዱ መታመሜን አይተው ባቲ ወረኢሉ መርሳና ውርጌሳ ትሞታለህ አሉ እኔ ግን አልሞትም መውደድ ያጸናኛል መታመን አክሞ ፍቅር ያኖረኛል አንቺ ሆዬ ለኔ ባቲ ያዘልቀኛል አሀሀሀሀሀሀ ኦሆሆሆሆሆ እኽል ውኃ ተውኩኝ መብል ምን ሊረዳኝ አንቺን በማጣቴ የፍቅር ፆም ጎዳኝ ደሴን ደጅ ጠናሁ ሐይቅ ዳር ቁጭ ብዬ በትዝታሽ ሐረግ ልቤን አንጠልጥዬ አምባሰል ዳመነ ገራዶ እያካፋ አድራለሁ ሳስብሽ ሆዴ እየተከፋ አይነጋልኝ ሌቱ ቀን አልመሽ ይለኛል ይህን ያንቺን ፍቅር ማን ሰው ያስጥለኛል መታመሜን አይተው ባቲ ወረኢሉ መርሳና ውርጌሳ ትሞታለህ አሉ እኔ ግን አልሞትም መውደድ ያጸናኛል መታመን አክሞ ፍቅር ያኖረኛል አንቺ ሆዬ ለኔ ባቲ ያዘልቀኛል አሀሀሀሀሀሀ ኦሆሆሆሆሆ