Teyim

Teyim

Michael Belayneh

Длительность: 4:59
Год: 2024
Скачать MP3

Текст песни

የመስከረም ዐደይ የበጋ ጨረቃ
መዉደድሽ አለልኝ እኔ አልሞትም በቃ
እንኳን ኖረሽልኝ ደስ እያሰኘሽኝ
ስቀሽ እያከምሽኝ አቅፈሽ እያደስሽኝ
ካንቺ ጋራ መሆን በምናብ ሽርሽር
መፍተሄ ስቃይ ነዉ ሕምን የሚሽር

የኔ ጠይም ውበት የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ የኔ ጠይም ቀለም

ለዓለም ማስታወሻ ከነፍስ ጋ እሚያርግ
ትህትናሽ ዕጣ ነው ለጽድቅ የሚዳርግ
አንዴ ወደ ናፍቆት አንዴ ወደ ትዝታ
ሳይሆን በትካዜ ሲሆን በፈገግታ
ባሳብ ወዲያ ወዲህ እመላለሳለሁ
አንቺን በልቤ ውስጥ በደግ አቆያለሁ

የኔ ጠይም ውበት የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ የኔ ጠይም ቀለም

ምን ያህል ባምንሽ ነዉ ምን ያህል ብወድሽ
ሆዴ ባዶ እስኪቀር ሁሉን የምነግርሽ
ናፍቆት ኩረፊያ ንዴት ተስፋ እርቅ ደስታ
ስዉ ታደርጊኛለሽ ከስር የተፈታ

የኔ ጠይም ውበት የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ የኔ ጠይም ቀለም

የኔ ጠይም ውበት የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ የኔ ጠይም ቀለም
የኔ ጠይም ውበት የኔ ጠይም ዓለም
የኔ ጠይም ዕጣ የኔ ጠይም ቀለም