Yefikr Mrchay

Yefikr Mrchay

Michael Belayneh

Длительность: 5:32
Год: 2008
Скачать MP3

Текст песни

የነገን ማወቅ ፈለግኩኝ
መጪዉን ማየት ናፈቅኩኝ
የፍቅር ምርጫዬ አንቺዉ ነሽ
ልቤን መንፈሴን የገዛሽ

ወሰንኩኝ ልረታ አስቤ
አካሌን መንፈሴን ሰብስቤ
በፍቅርሽ ህይወቴን ላኖረዉ
ላልመኝ ፍፁም ሌላ ሰዉ

ያሳለፍኩት ህይወት ብዙ ነዉ ልንገርሽ
ካየኋቸዉ ሁሉ አንቺ ትለያለሽ
ቃል ካፌ ባይወጣ ማዘን መደሰቴን
ፊቴን አይተሽ ብቻ ታዉቂያለሽ ስሜቴን

ከነገርሽ (ከነገርሽ)
ባህሪሽ ማርኮኛል
ካንቺ ልኖር (ካንቺ እንድኖር)
በፍቅር አስሮኛል
ዛሬ ባንቺ (ዛሬ ባንቺ)
በጣም ረክቻለሁ
ነገም አብረን (ነገም አብረን)
ሰላም አገኛለሁ

የነገን ማወቅ ፈለግኩኝ
መጪዉን አሁን ናፈቅኩኝ
የፍቅር ምርጫዬ አንቺዉ ነሽ
ልቤን መንፈሴን የገዛሽ
ወሰንኩኝ ልረታ አስቤ
አካሌን መንፈሴን ሰብስቤ
በፍቅርሽ ህይወቴን ላኖረዉ
ላልመኝ ፍፁም ሌላ ሰዉ

የፍቅርን ትርጉም ገልፀሸ አስተማርሽኝ
ካንቺ ደስታ የኔን እያስቀደምሽልኝ
ፍቅር ለካ ለራስ ማለት እንዳልሆነ
ስታደረጊዉ አይቶ ልቤ በቃ አመነ

ከነገርሽ (ከነገርሽ)
ባህሪሽ ማርኮኛል
ካንቺ ልኖር (ካንቺ እንድኖር)
በፍቅር አስሮኛል
ዛሬ ባንቺ (ዛሬ ባንቺ)
በጣም ረክቻለሁ
ነገም አብረን (ነገም አብረን)
ሰላም አገኛለሁ

ከነገርሽ (ከነገርሽ)
ባህሪሽ ማርኮኛል
ካንቺ ልኖር (ካንቺ እንድኖር)
በፍቅር አስሮኛል
ዛሬ ባንቺ (ዛሬ ባንቺ)
በጣም ረክቻለሁ
ነገም አብረን (ነገም አብረን)
ሰላም አገኛለሁ