Desse
Rophnan
4:34ልናገር ከመሸው ልደር ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር ልናገር ከመሸው ልደር ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር አልኩና ቃሌን ፈራሁ እንደገና ቃል ሰው ይሰብራልና ቃሌን ፈራሁ እንደገና ቃል ሰው ይገድላል ቃል ነበረ ከራስ መከረ በራሱ ምስል ሰውን ፈጠረ በፈጠረው ሰው ቃል አደረ ሰው ግን በአፉ ቃል ሰው ገደለ ቃል ነበረ ከራስ መከረ በራሱ ምስል ሰውን ፈጠረ በፈጠረው ሰው ቃል አደረ ሰው ግን በአፉ ቃል ሰው ሰበረ ሰው የቃል ስራ በቃል እጅ የተሰራ ስጋው ነው የቃል ጥራዝ በቃል አፍ የወጣ ነው ነፍሱ ሰው የቃል ትንፋሽ ህይወትም በኃይለቃል የበራች ናት የቃል ኩራዝ ከፀሐይ ከሰማይ ቃል ከቀደመ ከዓለም እንግዲህማ እውነቱ ከቃል በላይ ኃይል የለም ሰውም በተሰጠው ቃል ዓለምን ሁሉ ያጠፋል በሰው ያደረው ግን ቃል ዓለምን ደግሞ ያድናል አጀብ በዚህች ዓለም ሰውን የሚያነሳ ሰውን የሚጥል እንደ ቃል የለም ሰው በአፉ ቃል ሰውን ልክፍ ዓለም ጥምም ሰው በቃሉ መልካም ቢጽፍ ምድር ቅንን ቀና አጀብ በቃል ዓለም ሰው ባያውቀው የአንደበቱን የአፉን ቀለም ፈጣሪ ቃል በሰው ገላ እንዳደረ ሰው መልሶ በሰው ቃል ሰው ገደለ (ሰው ገደለ) ልናገር ከመሸው ልደር ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር አልኩና ቃሌን ፈራሁ እንደገና ቃል ሰው ይገድላልና ያ ደሃ ያ የሃብታም ቤቱ ዘበኛ ሲጠብቅ ቀንና ሌት የማይተኛ ላስተዋለ ልብ ላለ ላወቀው ያን የሃብታም ቤት ሳይሆን ቃሉን ነው የጠበቀው እኮ ቃል አይደለም ወይ መጀመሪያ ማንስ ነበረ? ቃል አይደለም ወይ የፈጠረ ሰማይ ከምድርን? ቃል አይደለም ወይ የወረደ ከድንግል ሊያድር? ቃሌን ብፈራው አይደለም ወይ ፈሪሐ እግዜር? ቃል ነበረ ከራስ መከረ በራሱ ምስል ሰውን ፈጠረ በፈጠረው ሰው ቃል አደረ ሰው ግን በአፉ ቃል ራሱን ገደለ የአፉን ያወቀ እግዜርን ከነፍሱን አስታረቀ ለእውነት ከአፉ ያፈለቀ የህይወት ፍሬን ዘርቶ አፀደቀ ሰው ቃሉ እንጂ የበላው ሆዱ ገነት ላያገባው ንጥቂያው ወይ ቅሚያው እኔ ልናገር ሽሚያው ላንወጣ ከማጡ የሚሉት ላያጡ ጣቶች አፍ አወጡ ፖስት ቃል ሳይመርጡ አፍ በዛ ቃል ጠፋ ፍቅር አንሶ ሆድ ከፋ ሁሉም አወቅኩኝ አለ ቃል ረክሶ ታች ሆነ ልናገር ከመሸው ልደር ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር የአንገቴን ክር ቃሌን አልፎ ላይገዛው ብር ከእውነት ዛፍ ስር እንኳን ሰው በቃሉ ያድራል ትል ጊዜም ዘመነ ደመረ ጨመረ አፍም ከአደባባይ ዋለ ቃልም ባከነ ፈጠነ ቀጠነ ሰው ወርዶ በፌስቡክ ማለ ዘመነ ስልክ ዘመነ ስማርት ዘመነ ታይፕ ዘመነ ጣት ዘመነ ላይክ ነው የላይክ ጥማት መስታወት ላይ የውሸት መዐት መስታወት ዋሸ መስታወት ዋሸ መስታወት ዋሸ መልክ አመለክን በፊልተር የታሸ መስታወት ዋሸ በጊዜው መስታወት ዋሸ የሃገር ሰው መስታወት ዋሸ ቃል እሸጥ ብሎ በቁሙ ሰው ቃዠ መስታወት መስታወት አየ የመስታወት ዝና በመስታወት ናኘ የመስታወት መልኳን በመስታወት ዳኘ የመስታወት ቃል ተሰብሮ ተገኘ ገበያ ገበያ ቃልን እንደ ሸቀጥ ቃል ከሚሸጥበት ውሃ ሲገድል ቀድሞ ያስቃል የሰው ልጅ አፍ ከባሕር ይጠልቃል ኢሞጂ ኢሞጂ ከአንገት በላይ ልከን ተወሻሽተን ግን በዓይን ላንተያይ ቆይ ቆይ በየት? ቆይ ቆይ በየት? በየት? ኢሞጂ ኢሞጂ ከአንገት በላይ ወደድኩሽ ይላታል ልብ ልኮ ልቧንም ሳያይ ቆይ በየት? ቆይ በየት? በየት? ልናገር ከመሸው ልደር ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሁሉም ቢቀር ልናገር ከመሸው ልደር ለእውነት ከሆነ ግዴለም ሞቼም ብቀር አልኩና ቃሌን ፈራሁ እንደገና ቃል ሰው ይሰብራልና ቃሌን ፈራሁ እንደገና ቃል ሰው ይገድላልና ቃል ነበረ ከራስ መከረ በራሱ ምስል ሰውን ፈጠረ በፈጠረው ሰው ቃል አደረ ሰው ግን በአፉ ቃል ሰው ገደለ ይሁን ለኔ ትውልድ ፎፍናን