ጌታ ኢየሱስ መድሃኒቴ
Tamirat Haile
4:48ሰርግና ፡ ምላሹ ፡ ድግሱ ፡ ቀለጠ ከትላንቱ ፡ አጀብ ፡ የዛሬው ፡ በለጠ የፍቅር ፡ ጨዋታው ፡ ከመቼው ፡ አለቀ የፍቺ ፡ ጥያቄ ፡ ፍርድ ፡ ቤት ፡ ዘለቀ ጭብጨባው ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዕልልታም ፡ ባልከፋ አስቸገረን ፡ እንጂ ፡ አንገት ፡ እያስደፋ አንገት ፡ እያስደፋ ትዳር ፡ ይከበር ፡ ቃልኪዳን ፡ ይጽና በመካከሉ ፡ አምላክ ፡ አለና መፋታትን ፡ እጠላለሁ ፡ ብሏልና ስብከት ፡ ሙያ ፡ ሆኖ ፡ ወንጌልም ፡ ለእንጀራ መዝሙሯ ፡ ጸሎቷም ፡ ሁሉም ፡ ተቸርችራ ገበያው ፡ ቀለጠ ፡ ቤተመቅደስ ፡ ደጃፍ ጌታ ፡ ተመልሶ ፡ እስኪያነሳ ፡ ጅራፍ ምን ፡ ትጠብቃለህ ፡ ሰብስብ ፡ ኮተትህን ያሸጥሃል ፡ ኋላ ፡ በኩርነትህን በኩርነትህን ወንጌል ፡ ይሰበክ ፡ በእውነት ፡ በጽድቅ በድብብቆሽ ፡ ቀኑ ፡ እንዳያልቅ መክሊት ፡ ሰጪ ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ሚጠይቅ ወንድሞች ፡ ተጣሉ ፡ በመሪነት ፡ ሰበብ ያውም ፡ በመድረኩ ፡ ጉድ ፡ እን ሽማግሌም ፡ ልግዛ ፡ መጋቢው ፡ ልንገሥ በኧረኞች ፡ ትግል ፡ መንጋ ፡ ሲታመስ በብዕር ፡ በቃላት ፡ ጦፈ ፡ ክርክሩ እስቲ ፡ መልሱልኝ ፡ የማነው ፡ ወንበሩ የማነው ፡ ወንበሩ መንጋው ፡ የኢየሱስ ፡ የሞተለት የበረቱን ፡ ቁልፍ ፡ አስረክቡት የእኛ ፡ ጥሪ ፡ ዝቅታ ፡ ነው ፡ ሎሌነት ነጭ ፡ ጥቁር ፡ ቀለም ፡ መለየት ፡ አቅቶት ድንበር ፡ የጣሰ ፡ ይላል ፡ ምናለበት ጽድቅ ፡ ከአመጽ ፡ ጋር ፡ ብርሃን ፡ ከጨለማ አምላክ ፡ ያጣላውን ፡ ማን ፡ አለህ ፡ አስማማ ይልቅ ፡ ከዓለም ፡ ተለይ ፡ ውጣ ፡ ተቀደስ የትም ፡ እየረገጥክ ፡ ቤቱን ፡ አታርክሲ ቤቱን ፡ አታርክሲ እልፍ ፡ በል ፡ ውጣ ፡ ተለይ ስሙ ፡ ተጠርቷል ፡ በአንተ ፡ ላይ የሚመጣ ፡ ሙሽራ ፡ አለህ ፡ ከሠማይ ሆድም ፡ ለመብል ፡ ነው ፡ መብልም ፡ ለሆድ ሁሉም ፡ ይጠፋሉ ፡ ብንወድም ፡ ባንወድ አንዳንዴም ፡ በመጾም ፡ ጐሽም ፡ ሥጋህን አብልቶ ፡ ከሚዘርፍ ፡ አስጥል ፡ ፀጋህን እንቅልፍም ፡ አይብዛ ፡ አርግለት ፡ ገደብ ጸሎት ፡ አይረሳ ፡ ቃሉም ፡ ይነበብ ቃሉም ፡ ይነበብ ተነስ ፡ ተጋደል ፡ ጸንተህ ፡ ተዋጋ ያበረታሃል ፡ የአምላክህ ፡ ፀጋ የትም ፡ መቼም ፡ ጌታ ፡ እንዳለ ፡ አትዘንጋ