Endiet
Tibebu Workyie
5:37ተለያዩ ሲባል ኧረ ሰዉ ምን ይለናል እሺ የኛስ ይሁን የሰማ ሰው ምን ይለናል ግዴለም አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል እባክሽ አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል ተለያዩ ሲባል ኧረ ሰዉ ምን ይለናል እሺ የኛስ ይሁን የሰማ ሰው ምን ይለናል ግዴለም አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል እባክሽ አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል ያየን እስኪደነቅ ማመን እስኪያቅተው እንዲህም አይነት ፍቅር አለ ወይ እስኪል ሰው ሳይቸግረን ያኔ ከዓይን ውስጥ ገብተናል ጥላው ሄደች ቢባል አሁን ሰው ምን ይላል እመነኝ ስትዪኝ ጎዳናው ሰምቶሻል እንደኔ በደስታ ሳር ቅጠሉ አይቶሻል ተለያዩ ሲባል መርዶውን አይወዱም ቅጠሉም ይረግፋል ተይ ያዝናሉ እንደጉም ፍቅራችንን ተመልክቶ ካይን ያውጣችሁ ያኔ ያለን የሰማ ቀን ይተክዛል ድንገት ወረት ሲለያየን የለመደሽ መስኪን ቤቴ ተይ ጭር ይላል ከሄድሽበት እኔም ውስጤ ይሰበራል እባክሽን አስቢበት ተለያዩ ሲባል ኧረ ሰዉ ምን ይለናል እሺ የኛስ ይሁን የሰማ ሰው ምን ይለናል ግዴለም አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል እባክሽ አትሂጂ አብሮ መኖር ይሻለናል በፍቅር የሚያውቀን ሲያጣሽ ፊቱ ጠቁሮ እንደድሮው መስሎት ምነው ያለ ወትሮ ብቻህን የት ሄደች ቢለኝ ሲያይ ከስዬ መመለስ አልችልም ጥላኝ ሄደች ብዬ በትንሽ ትንሹ አድርገው ከወሰዱት አይገድልም ይባላል መርዝም ከለመዱት ባይሆን ቀስ በቀስ ውስጤን እንዳይከብደው ባክሽ ትንሽ ቆዪ ስቃዩን ብለምደው ፍቅራችንን ተመልክቶ ካይን ያውጣችሁ ያኔ ያለን የሰማ ቀን ይተክዛል ድንገት ወረት ሲለያየን የለመደሽ መስኪን ቤቴ ተይ ጭር ይላል ከሄድሽበት እኔም ውስጤ ይሰበራል እባክሽን አስቢበት