Notice: file_put_contents(): Write of 629 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Tsehaye Yohannes - Semonun | Скачать MP3 бесплатно
Semonun

Semonun

Tsehaye Yohannes

Альбом: Sakilgne
Длительность: 4:53
Год: 2007
Скачать MP3

Текст песни

በጭራሽ ምንም አልገባህ አለኝ ሰሞኑን እኔ
ምን እግር ጣለና አመጣት ደግሞ ገርሞኛል እኔ
በህልሜም በእዉኔ እሷ ብቻ ናት ሰሞኑን በአይኔ
በህልሜም በእዉኔ እሷ ብቻ ናት ሰሞኑን በአይኔ
በጭራሽ ምንም አልገባህ አለኝ ሰሞኑን እኔን
ምን እግር ጣለና አመጣት ደግሞ ገርሞኛል እኔን
በህልሜም በእዉኔ እሷ ብቻ ናት ሰሞኑን በአይኔ
በህልሜም በእዉኔ እሷ ብቻ ናት ሰሞኑን በአይኔ
ምን ሆና ምን አገኛት ይሆን እንዴትስ አሰብኳት ለመሆኑ
ስወጣም ስገባም እሷዉ ናት ከአይኔ ጠፍታ አታዉቅም ከሰሞኑ
ማን ያዉቃል የጠበቃት ልቤ እስካሁን ሳይረሳት ሳይበገር
መልሶ በወሰዳት እግሯ ያመጣትስ ቢሆን የአምላክ ነገር
ጥላኝ ከሄደች በስንት አመቱ ከአይኔ ከራቀች
እሄዉ ሰሞኑን እስከሚገርመኝ ሁሌ በአይኔ ነች
ጥላኝ ከሄደች በስንት አመቱ ከአይኔ ከራቀች
እሄዉ ሰሞኑን እስከሚገርመኝ ሁሌ በአይኔ ነች
ሰሞኑን ከአፌ አልወርድ ያለችዉ ለመዉዴ መፍቻ
ቤቴን ለማፍረስ ልትመጣ አስባ ብቻ እንዳይሆን ብቻ
ሰሞኑን ከአፌ አልወርድ ያለችዉ ለመዉዴ መፍቻ
ቤቴን ለማፍረስ ልትመጣ አስባ ብቻ እንዳይሆን ብቻ
በጭራሽ ምንም አልገባህ አለኝ ሰሞኑን እኔ
ምን እግር ጣለና አመጣት ደግሞ ገርሞኛል እኔ
በህልሜም በእዉኔ እሷ ብቻ ናት ሰሞኑን በአይኔ
በህልሜም በእዉኔ እሷ ብቻ ናት ሰሞኑን በአይኔ
በህልሜም በእዉኔ እሷ ብቻ ናት ሰሞኑን በአይኔ
ከፍቅር ኑሮን አስቀድማ ጥላኝ ከነጐደች በጠዋቱ
ሳላዉቀዉ ብዙ ዘመን ሆነዉ ሄደ ቀን ቆጠረ ራቀ አመቷ
ሰሞኑን በአይኔ ላይ እሷዉ ናት ከአፌ ላይ አትወርድም እስኪደንቀኝ
አሁንም በፍቅር ከእኔ ጋር አጠገቤ ያለች እስኪመስለኝ
ጥላኝ ከሄደች በስንት አመቱ ከአይኔ ከራቀች
እሄዉ ሰሞኑን እስከሚገርመኝ ሁሌ በአይኔ ነች
ጥላኝ ከሄደች በስንት አመቱ ከአይኔ ከራቀች
እሄዉ ሰሞኑን እስከሚገርመኝ ሁሌ በአይኔ ነች
ሰሞኑን ከአፌ አልወርድ ያለችዉ ለመዉዴ መፍቻ
ቤቴን ለማፍረስ ልትመጣ አስባ ብቻ እንዳይሁን ብቻ
ሰሞኑን ከአፌ አልወርድ ያለችዉ ለመዉዴ መፍቻ
ቤቴን ለማፍረስ ልትመጣ አስባ ብቻ እንዳይሁን ብቻ
ሰሞኑን ከአፌ አልወርድ ያለችዉ ለመዉዴ መፍቻ
ቤቴን ለማፍረስ ልትመጣ አስባ ብቻ እንዳይሁን ብቻ
ሰሞኑን ከአፌ አልወርድ ያለችዉ ለመዉዴ መፍቻ
ቤቴን ለማፍረስ ልትመጣ አስባ ብቻ እንዳይሁን ብቻ