Notice: file_put_contents(): Write of 582 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Yema - Lomeye | Скачать MP3 бесплатно
Lomeye

Lomeye

Yema

Альбом: Yedega Sew
Длительность: 5:36
Год: 2024
Скачать MP3

Текст песни

በፍቅር መንገድ ላይ ሰከን ብዬ ረጋ
ሸተት አደረገኝ ድንገት ብዘናጋ
ጥርስ ዓይኑ መች ሆነ የረታኝ ባንዳፍታ
አደናቅፎ የጣለኝ የአንገቱ ስር ሽታ

ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ

ትንፋሽህ ጠረንህ ከመደቤ ቀርቶ
አንድ አንተን ይለኛል በመውደድህ ሳስቶ
ወይባ ቡክቡካ አደስ ነው ፍቅርህ
ውልብ ይልብኛል ፈልጌ ባጣህ
ወይባ ቡክቡካ ሽቶ ነው ፍቅርህ
ውልብ ይልብኛል ፈልጌ ሳጣህ

አምና ባይኔ ታመህ (ገላ ገላ) አይቼህ ብረታ (መላ መላ)
ዘንድሮ ልሞት ሰርስሮኝ በሽታ
ፈልግልኝ ዘዴ (ገላ ገላ) ፈልግልኝ መላ (መላ መላ)
ባየር በንፋሱ ላከው ያንተን ገላ

ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ

ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ

ያለፍክበት ሁሉ መዓዛህ ያውዳል
የፍቅርህ እንፋሎት አተኩሶ ይፋጃል
ወገርት ነው ጥንጁት ፍቅርህ ጠጅ ሳር
ይጤሳል ይነዳል ከሆድ ሆዴ ስር
ወገርት ነው ጥንጁት ፍቅርህ ጠጅ ሳር
የሚጤስ የሚነድ ከአንጀት ከሆድ ስር

አድራሻህን ባላውቅ (ገላ ገላ) ከቶ አያሳስብህ (መላ መላ)
ይምረኝ የለም ወይ ጣፋጭ ጠረንህ
ምን ጉም ቢጋርደው (ገላ ገላ) ሰፈርህ ርቆ (መላ መላ)
ፍቅርህ ደጄ ደርሷል አየሩን ሰንጥቆ

ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ

ከእንጨት ይነጠራል (ገላ ገላ) እጣንና ሽቶ (መላ መላ)
ያንተስ ከገላህ ነው ከወዝህ ተቀድቶ
ከወዝህ ተቀድቶ (ገላ ገላ) አሽገህ በመላ (መላ መላ)
ላክልኝ ልነስነስ ልራስ ባንተ ገላ

ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ሎምዬ ሎምዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ
ጥሜን ቁረጥልኝ ከደረትህ ውዬ