Notice: file_put_contents(): Write of 627 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Yilma Hailu - Kiyamayew | Скачать MP3 бесплатно
Kiyamayew

Kiyamayew

Yilma Hailu

Альбом: Tewahedo #2
Длительность: 5:42
Год: 1993
Скачать MP3

Текст песни

ፈያታዊ ዘየማን አምላኩን ለመነ
በቀኝ ያቆመው ዘንድ ጌታን ተማጸነ
ወንበዴ ብሆንም ሽፍታ ወንጀለኛ
መምጣትህን አሰብኩ ለድህነት ወደኛ

አልሰማሁም እኔ የነቢያትን ቃል
አላወቅኩም በእርግጥ አብሮኝ እስኪሰቀል
ኢሳይያስ ሲናገር ዳዊት ሲመሰክር
የመሲሁን መምጣት አልሰማሁም ነበር
አዝ
በመስቀል ላይ ሳለ አምላኬን ለየሁት
ትሁት ነበር ፍጹም በደል የሌለበት
ስለ በደላችን እኛ ተሰቅለናል
እሱ ግን በማን ላይ ወንጀልን ፈጽሟል
አዝ
ጨረቃ ደም ሆና ፀሐይዋ ስትጨልም
ከዋክብት ረግፈው ሰማይ ሲያጉረመርም
አምላክ መሰቀሉን ተፈጥሮ ነግራኝ ነው
በመንግሥትህ ጌታ አስበኝ የምለው
አዝ
አወይ ቀያፋ ሆይ አወይ ሀና ሆይ
ደስ ብሏችሁ ዋለ በጌታ ስቃይ
ተፈጥሮ ምስክር ሆኖ ሲያስተምራችሁ
እንዴት አላመነም ደንዳናው ልባችሁ