Notice: file_put_contents(): Write of 640 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Bereket Tesfaye - Yewuha Bereha | Скачать MP3 бесплатно
Yewuha Bereha

Yewuha Bereha

Bereket Tesfaye

Альбом: Memihiru
Длительность: 5:21
Год: 2023
Скачать MP3

Текст песни

ብዙ ፍጥረት ያለው ባህር ውቅያኖሱ
ለየብስ ሩብ ሰጥቶ ቀሪውን መልበሱ
ላጥፋ ካለ አጥፊ ጡንቻ አለው ፈርጣማ
ካንዱ ጌታ በቀር ማንንም አይሰማ
ጥም አርኪ ይመስላል ግን ለጠማው ደሃ
ውስጡ ስለሌለው ለመጠጥ የሚሆን አንድ ብርጭቆ ውሃ
ሰነፍ መርከበኛ ውቅያኖሱ ዳር
ሚጠጣውን ሳይዝ መጓዝ ቢጀምር
ውሃ መሃል ደርሶ ውሃ ይጠማዋል
ውሃ በረሃ ላይ በውሃ ጥም ይሞታል

አንድ ጉድጓድ አለች በጣም ትንሽዬ
ህፃን ነህ አዋቂ ጨዋ ነህ ዱርዬ
ሳትል ሳታዳላ ሁሉን ታጠጣለች
ይህን ንፁህ ውሃ ታመነጨዋለች
ጠቢቡ ገበሬ እሷ ዳር ይዘራል
ዘሩም ምንጯን ነክቶ ማን ደርቆ ይቀራል
ጌታ ኢየሱስን በዕምነቱ የነካ
ከህይወት ውሃ ምንጭ ጠጥቶ እረካ

ስንት ምስኪን አለ ሳይተኛ ሚያነጋ
ነፍሱ ምትገረፍ በጥማት አለንጋ
እግዚአብሔር ነፍሱን ነይ ላርካሽ ቢላት
የእግዚአብሔርን ሳይሆን ለነፍሱ ሆዱን ሰማላት
ጌታ በሌለበት በዛ ባዶ ቦታ
ምኑንም ቢከቱ አይሰጥም እርካታ
ሰማይ እና ምድር ባንዴ ተጠቅልሎ
የኢየሱስን ቦታ አይሞላውም ችሎ

የተከበበ በማይጠጣ
በዓለም ያለ ሰው ኢየሱስን ያጣ
በጀልባ እንደጠፋ ውቅያኖስ ላይ
ኢየሱስ የሌለው ሰው እሱ አይደል ወይ
ተበልቶ ተጠጥቶ የለም እርካታ
ኑሮ ማለት ሃሩር ከሌለው ጌታ

ኦ (ዳግመኛ አልጠማኝም አንዴ ጠጥቼው)
(ጎዶሎ የለኝም ውስጤ ሙሉ ነው)
አልጠማኝ እኔ አልጠማኝም(ዳግመኛ አልጠማኝም አንዴ ጠጥቼው)
(ጎዶሎ የለኝም ውስጤ ሙሉ ነው)