Meche Eresahu
Daniel Amdemichael
4:59ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አንተ ፡ የሁሉ ፡ መድሃኒት በቸርነት ፡ እየደገፍክ ፡ ታኖረኛለህ ፡ በሕይወት ምስክር ፡ ነኝ ፡ ለሰራኸው ፡ ብዙ ፡ ተዓምር ፡ አይቼአለሁ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ስለ ፡ ፍቅርህ ፡ በየዕእለቱ ፡ እደነቃለሁ አዝ፦ ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ምህረት ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ሥራ ያኖረኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፣ ያኖረኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ አቁሞኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፣ አቁሞኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x) ቀኑን ፡ ስትጠብቀኝ ፡ ውለህ ፡ ጌታ ፡ ሌሊቱን ፡ አትተኛ በመውጣቴ ፡ በመግባቴ ፡ ሆነኸኛል ፡ ቸር ፡ እረኛ መች ፡ ያልቅና ፡ የአንተ ፡ ሥራ ፡ በየዓይነቱ ፡ ብዘረዝር ቃል ፡ አጣሁ ፡ እጄን ፡ በአፌ ፡ ጭኜ ፡ ከመደነቅ ፡ በቀር አዝ፦ ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ምህረት ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ሥራ ያኖረኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፣ ያኖረኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ አቁሞኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፣ አቁሞኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)