Yelibe Zema
Dibekulu
4:25ልድረስሽ እንደ ግጥም ላፍልቅሽ እንደ ዜማ አለም አጀብ ያለው ፍፁም ያልተሰማ እንደ አእዋፋት ቃና ጆሮ የሚሰማማ እንደ ጣና ደንገል ውብ ባለ ግርማ በቀና የልብሽ ጎዳና ነውና ድብቅ ገናና አንቺ ከአውድማው እኔ ከአምባው ላይ ክራር ስደረድር ተከፍቶ ሰማይ ቀለማትን ረጨ ስለኛ ጉዳይ ከእርሱ የተቸርሽኝ የምድሩ ነዋይ በቀና የልብሽ ጎዳና ነውና ድብቅ ገናና በቀና የልብሽ ጎዳና ነውና ድብቅ ገናና ከሀቀኞቹ ቁና ጎርፈሽ እንደ ጅረት በታላቅ ወደቀ የሸንጋይ መሰረት አወይ ትህትናሽ ምሉዕ ያለወረት ሲያወጉት መሰለ የብልሃት ተረት አወይ ትህትናሽ ምሉዕ ያለወረት ሲያወጉት መሰለ የብልሃት ተረት