Yebezegnal
Endale Woldegiorgis
5:50ድንቅ ፡ ነህ (Denq Neh) ጌታ ፡ ፈጣሪዬ ፡ ስለ ፡ አፈጣጠሬ ስለሚያስደንቀው ፡ ስለ ፡ አካል ፡ ክፍሌ ላመሰግንህ ፡ እፈልጋለው ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ሆኜ ፡ ተፈጥሪያለው ፪X ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ ፪X የማመስገኛ ፡ ምክንያት ፡ ከሆነ ከቁጥር ፡ በላይ ፡ እኔ ፡ ጋር ፡ አለ እግሬ ፡ ሲራመድ ፡ ሚዛን ፡ ጠብቆ ዓይኔም ፡ ሲያይልኝ ፡ ቅርብም ፡ አርቆ በራስ ፡ ቅሌ ፡ ላይ ፡ ሲበቅል ፡ ፀጉሬ ጣቶቼ ፡ ላይ ፡ ሲያድግ ፡ ጥፍሬ ውበት ፡ አላቸው ፡ በየቦታቸው ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራሃቸው ፪X ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ ፪X ሰው ፡ ሰውን ፡ ቢሰራው ቢያበጀው ፡ እስትንፋስ ፡ ቢሰጠው የሚከፍለው ፡ አጥቶ ሁሉም ፡ ሰው ፡ መኖር ፡ በተሳነው ይተመን ፡ ቢባል ፡ በዋጋ ፡ የአካል ፡ ክፍሌ በዓለም ፡ ያለው ፡ ሃብት ፡ በሙሉ ፡ አይመጥን ፡ ለኔ እንዃን ፡ ሁሉንም ፡ ይቅርና ፡ አንዱንስ ፡ እንኳ መፍጠር ፡ ያልቻለው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ እንዴት ፡ ይመካ ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ ፪X በሚጥም ፡ ዜማ ፡ የሚያዜመው ፡ የአንተን ፡ ዝማሬ ገንዘብ ፡ ሊገዛው ፡ አይችል ፡ ይህ ፡ አንደበቴ ፪X ጌታ ፡ ፈጣሪዬ ፡ ስለ ፡ አፈጣጠሬ ስለሚያስደንቀው ፡ ስለ ፡ አካል ፡ ክፍሌ ላመሰግንህ ፡ እፈልጋለው ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ሆኜ ፡ ተፈጥሪያለው ፪X ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ ፪X