Notice: file_put_contents(): Write of 632 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Temesgen Markos - Tewelede | Скачать MP3 бесплатно
Tewelede

Tewelede

Temesgen Markos

Альбом: Sew Biteyek
Длительность: 4:03
Год: 2019
Скачать MP3

Текст песни

የእግዚአብሔር ፈቃድ በልጁ ሊፈጸም
ራሱን ዝቅ አድርጐ ወረደ ለዓለም
በምድር ሊሰማ ሰላምና ደስታ
ከድንግል ማሪያም ተወለደ ጌታ

አዝ፦ ተወለደ
ተወለደ

እነሆ የምስራች እነሆ የምስራች
ዛሬ በዳዊት ከተማ
እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ
ተወለደ ተወለደ

እረኞች ለማየት እጅጉን ጓጉለት
ሰባ ሰገል መተው ወድቀው ሰገዱለት
የፍጥረታት ጌታ የዓለም ሁሉ ንጉሥ
ከአብ ሊያስታርቀን ተወለደ ኢየሱስ

አዝ፦ ተወለደ
ተወለደ

መላዕክት አበሰሩ የምስራቹን ቃል
ዛሬ በቤቴልሄም ወንድ ልጅ ተወልዷል
ምድር ዕልል ትበል ታሰማ ምሥጋና
ሕዝቡን የሚታደግ መሲህ መጥቷልና

አዝ፦ ተወለደ
ተወለደ

እነሆ የምስራች እነሆ የምስራች
ዛሬ በዳዊት ከተማ
እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ
ተወለደ ተወለደ