Kezebiye
Theodros Kassahun
5:54እኔስ የለኝ ጓደኛ ባይተዋር ነኝ ብቸኛ እኔ አልሻም ሰው ለምኔ ከኔ ወዲያ ለኔ እኔስ የለኝ ጓደኛ ባይተዋር ነኝ ብቸኛ እኔ አልሻም ሰው ለምኔ ከኔ ወዲያ ለኔ ይበጀኛል ብዬ ሰው አምኜ ነበር ከመሸ ላይገኝ ወዳጅ እና ጀምበር በሀዘን በመከራ መች አብሮ ይዘልቃል ኪስ የገዛው ወዳጅ ቀን አይቶ ይርቃል በቃኝ በቃኝ በቃኝ ቁረጥ ሆዴ ምነው ዛሬስ እርም አትልም እንዴ ለክፉ ቀን ደራሽ ተቆርቋሪ ጠያቂ 'ማያገኝ ፆም አዳሪ በደራበትማ ሰው መች ጠፋ ይቆጠራል ወዳጅ ቀን ሲከፋ ሰው ቢለወጥ ሰው ቢከዳ ልብ አይሆንም ባዳ ሰው ቢለወጥ ሰው ቢከዳ ልብ አይሆንም ባዳ እኔስ የለኝ ጓደኛ ባይተዋር ነኝ ብቸኛ እኔ አልሻም ሰው ለምኔ ከኔ ወዲያ ለኔ እኔስ የለኝ ጓደኛ ባይተዋር ነኝ ብቸኛ እኔ አልሻም ሰው ለምኔ ከኔ ወዲያ ለኔ ምን አብረው ቢበሉ እንደራስ ቢወዱ የውስጡ አይታይም ሰው ዋሻ ነው ሆዱ አይባል ለከርሞ እንደዘሩት አርሰው ቀን ሲጥል ይጥላል መቼም የዛሬ ሰው በቃኝ በቃኝ በቃኝ ቁረጥ ሆዴ ምነው ዛሬስ እርም አትልም እንዴ አርም ብዬ ወዳጅ ከሰው ርቄ ልቤን እያሸሸሁ ስኖር ስቄ ግኑ ልቤ ሰው ይለኛል ከራስ ወዲያ ዘመድ የት ይገኛል ሰው ቢለወጥ ሰው ቢከዳ ልብ አይሆንም ባዳ ሰው ቢለወጥ ሰው ቢከዳ ልብ አይሆንም ባዳ