Abat Alegn
Yosef Kassa
6:33በመንገዴ ፡ ስሄድ ፡ ስራመድ ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና እግሮቼ ፡ በቤትህ ፡ ጸንተው ፡ ዓይኔ ፡ ግን ፡ ሳይበራ የሚሄደው ፡ የሚመጣው ፡ ሲያዳክመው ፡ ፡ ልቤን የቆምኩኝ ፡ ያለሁኝ ፡ መስሎኝ ፡ እያንገዳገደኝ አልገባኝም ፡ ነበር ፡ የልቦና ፡ ዓይኔ ፡ ታውሮ ምድር ፡ ምድር ፡ አለ ፡ የከበረውን ፡ ሰማይን ፡ ጥሎ ቃልህን ፡ ስሰማ ፡ ልቤ ፡ ተደስቶ ለጊዜው ፡ ነበረ ፡ በስሜት ፡ ተገፍቶ ነፋስና ፡ ጐርፉ ፡ ሊፈትነኝ ፡ መጣ ይታወቀኝ ፡ ጀመር ፡ ከመንገድ ፡ ስወጣ ቢበራማ ፡ በቃልህ ፡ ቢጸና ፡ ዓይኔ ፡ ቢበራ ቢበራማ ፡ ጸንቶ ፡ ይቆም ፡ ነበር ፡ ፍሬ ፡ እያፈራ ቢበራማ ፡ ቅርንጫፍ ፡ ከግንዱ ፡ ከተጣበቀ ቢበራማ ፡ ያስታውቃል ፡ መልኩ ፡ አንተን ፡ ያወቀ ዓይኖቼን ፡ አብራ ፡ ክፈት ፡ ዓይኔን እነደ ፡ እኔ ፡ ሳይሆን ፡ እንዳንተ ፡ እንዳይ በመንገዴ ፡ ስሄድ ፡ ስራመድ ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና እግሮቼ ፡ በቤትህ ፡ ጸንተው ፡ ዓይኔ ፡ ግን ፡ ሳይበራ የሚሄደው ፡ የሚመጣው ፡ ሲያዳክመው ፡ ፡ ልቤን የቆምኩኝ ፡ ያለሁኝ ፡ መስሎኝ ፡ እያንገዳገደኝ አልገባኝም ፡ ነበር ፡ የልቦና ፡ ዓይኔ ፡ ታውሮ ምድር ፡ ምድር ፡ አለ ፡ የከበረውን ፡ ሰማይን ፡ ጥሎ ሲዘነጋ ፡ ለቤ ፡ የሰማዩን ፡ ቤቱን በዚህ ፡ ምድር ፡ሲኖር ፡ እንግዳ ፡ መሆኑን አይጐመጅም ፡ ነበር ፡ ለምድራዊው ፡ ኑሮ የሰማዩን ፡ ዓለም ፡ አንዴ ፡ ቢያየው ፡ ኖሮ ቢበራማ ፡ የተጠራበትን ፡ የክብር ፡ ተስፋ ቢበራማ ፡ የዘላለም ፡ እርስት ፡ ከቶ ፡ ማይጠፋ ቢበራማ ፡ ዓይኖቼ ፡ ተከፍቶ ፡ ይህንን ፡ ቢያይ ቢበራማ ፡ ይናፍቃል ፡ ልቤ ፡ ወደ ፡ ሰማይ ዓይኖቼን ፡ አብራ ፡ ክፈት ፡ ዓይኔን እነደ ፡ እኔ ፡ ሳይሆን ፡ እንዳንተ ፡ እንዳይ ልመናዬ ፡ ይሄ ፡ ነው አብራው ፡ ዓይኔን