Kidus
Endale Woldegiorgis
6:11የማታረጀው ፡ ማትቀደደው ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት:ግርማ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ 2X አንተን ፡ ለብሶ ፡ ተጐናፅፎ እራቁቱን ፡ ማንስ ፡ ቀርቶ የለበሰህ ፡ ከበረ ፡ እንጂ መቼ ፡ ቆመ ፡ ውርደት ፡ ደጅ አንተን ፡ ያለ ፡ የታደለ ፡ እራቆቱ ፡ ተሸፈነ 2X ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ 2X ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ሚለበስ ፡ ሁሉ የማያዛልቅ ፡ ቅጠል ፡ መሆኑ የተረዳ ፡ ሰው ፡ ሌላውን ፡ አውልቆ አንተን ፡ ሲለብሰህ ፡ አዳኙን ፡ አውቆ የሞትን ፡ ነፋስ ፡ ብርድን ፡ አይፈራ ፡ የዘላለሙን ፡ ለብሶሃልና 2X ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ 2X የማታረጀው ፡ ማትቀደደው ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት ፡ ግርማ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ 2X