Ameseginalehu
Samuel Negussie
6:10የብቸኝነቴ ወራት ወዳጄ ሁሉም ገሸሽ ሲል ሲርቅ ከአጠገቤ በመልካሙ ምክርህ በቃልህ ደግፈኸኝ እዚህ ያደረስከኝ ኢየሱስ አንተ ነህ አንተ ነህ የራራህልኝ አንተ ነህ የተሸከምከኝ አንተ ነህ ዘይት ቀብተህ አንተ ነህ ፊትህ ያቆምከኝ አንተ ነህ የደረስክልኝ አንተ ነህ እኔን ያየኸኝ አንተ ነህ ፈፅሞ አልረሳም አንተ ነህ ሰው ያደረከኝ ህልም ህልም ይመስለኛል ዞር ብዬ ሳየው የትላንትናውን ያለፍኩት ባንተ ነው አንተ ቀድመህ ፊቴ ባይቀና መንገዴ እንዴት እሆን ነበር ለብቻዬ ባትራራልኝ ውዴ ትላንትን አልፌ ዛሬ ላይ ስደርስ ሁሉን እንዳለፍኩት በራሴ ብርታት እኔ አይሆንልኝም ማሳየት እራሴን ደብቄው ፍቅርህን ሰው የመሆን ምክንያቴን ኢየሱስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም ወዳጄ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እንደራራህልኝ እኔስ አልረሳውም ብዙ እንደደገፍከኝ እኔስ አልረሳውም እንደተሸከምከኝ እኔስ አልረሳውም ፍቅር እንዳሳየኸኝ እኔስ አልረሳውም በልቤ ተፅፎ ዘላለም ይኖራል ፍቅር ምህረትህ የኔ ወዳጅ እንዴት ይረሳኛል ፀጋህን አብዝተህ እየደጋገፍከኝ ለአንዴም ሳይቀየር አባ ፊትህ ዛሬን አደረስከኝ አይረሳም አይረሳም ኢየሱስ የዋልክልኝ በእያንዳንዱ ህይወቴ አሻራህ አለብኝ መልካምነትህን ሳወራ እኖራለው ባንተ ሰው መሆኔን ፍጥረት ሁሉ ይስማው ኢየሱስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም ወዳጄ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እንደራራህልኝ እኔስ አልረሳውም ብዙ እንደደገፍከኝ እኔስ አልረሳውም እንደተሸከምከኝ እኔስ አልረሳውም ፍቅር እንዳሳየኸኝ እኔስ አልረሳውም አልረሳውም(2×) እኔ አልረሳውም አልረሳውም አልረሳውም(2×) እኔ አልረሳውም አልረሳውም