Notice: file_put_contents(): Write of 629 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Theodros Kassahun - Tizibit | Скачать MP3 бесплатно
Tizibit

Tizibit

Theodros Kassahun

Альбом: Teddy
Длительность: 5:44
Год: 2002
Скачать MP3

Текст песни

ፍቅሬን ችላ ብለሽ ጣል አርገሽ መውደዴን
ስታስከፊኝ ርቀሽ ቅር ቢለው ሆዴን
አይወጣኝም ክፉ
ትዝብት ነው ትርፉ
ፍቅሬን ችላ ብለሽ ጣል አርገሽ መውደዴን
ስታስከፊኝ ርቀሽ ቅር ቢለው ሆዴን
አይወጣኝም ክፉ
ትዝብት ነው ትርፉ
አምና እና ካቻምና ምን ብለሽኝ ነበር
ቃልሽ እንደወረት ወድቆ ባይሰበር
ቃልሽ እንደዘበት ወድቆ ባይሰበር
ለቃልኪዳን አድረሽ ካልታመንሽ እንደ እኔ
ለፍቅርም ጡር አለው ለፅድቅም ኩነኔ
ለፍቅርም ጡር አለው ለፅድቅም ኩነኔ
ፍቅሬን ችላ ብለሽ ጣል አርገሽ መውደዴን
ስታስከፊኝ ርቀሽ ቅር ቢለው ሆዴን
አይወጣኝም ክፉ
ትዝብት ነው ትርፉ
ክፉ አይውጣው እንጂ ሰው ያዝናል ሲከፋ
ብዙ ቢችል አንጀት ሆድ ከሃገር ቢሰፋ
ብዙ ቢችል አንጀት ሆድ ከሃገር ቢሰፋ
የፍቅርን ገበታ ሰው አብሮ ሰንቆ
ተሸሽጎ ላይችል ምን አስበላው ሰርቆ
ተሸሽጎ ላይችል ምን አስበላው ሰርቆ
ፍቅሬን ችላ ብለሽ ጣል አርገሽ መውደዴን
ስታስከፊኝ ርቀሽ ቅር ቢለው ሆዴን
አይወጣኝም ክፉ
ትዝብት ነው ትርፉ
ምን አንጀት ቢከፋም ጭንቅ እያተረፈ
መለየት ይከብዳል አብሮ ካሳለፈ
መለየት ይከብዳል አብሮ ካሳለፈ
መራቅ እያሳሳው ለብቻ መልመዱ
ከአንጀት የወደደ መች ይቆርጣል ሆዱ
ከአንጀት የወደደ መች ይቆርጣል ሆዱ
ፍቅሬን ችላ ብለሽ ጣል አርገሽ መውደዴን
ስታስከፊኝ ርቀሽ ቅር ቢለው ሆዴን
አይወጣኝም ክፉ
ትዝብት ነው ትርፉ
ፍቅሬን ችላ ብለሽ ጣል አርገሽ መውደዴን
ስታስከፊኝ ርቀሽ ቅር ቢለው ሆዴን
አይወጣኝም ክፉ
ትዝብት ነው ትርፉ
አይወጣኝም ክፉ
ትዝብት ነው ትርፉ